በአንድ የግብር ዓመት የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ የሌለበት ግብር ከፋይ ግብር የሚከፈልበት ገቢ በሚሰላበት ጊዜ የሚከተሉት ወጪዎች በተቀናሽ ይያዛሉ፡-
ታክስን ሳይጨምር ለመሬቱ ወይም ከተከራየው ቤት ጋር በተገናኘ ግብር ከፋዩ ለመንግስት ወይም ለከተማ አስተዳደር በግብር ዓመቱ ውስጥ የከፈላቸው ክፍያዎች፣
ለቤቶች፣ለቤት ዕቃና መሳሪያ ማደሻ፣ መጠገኛና ለእርጅና መተኪያ የሚሆን ከቤት ዕቃና ከመሣሪያ ኪራይ ከሚገኘው ጠቅላላ ገንዘብ ላይ 50% በመቶ ተቀናሽ ይፈቀድለታል፡፡
ከላይ የተመለከተው 50% ተቀናሽ በማናቸውም ሁኔታ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ላለባቸው ግብር ከፋዮች ተፈፃሚ አይሆንም፡፡
የሂሳብ መዝገብ የሚይዝ ግብር ከፋይ በግብር ዓመቱ ግብር የሚከፈልበት ገቢ በሚሰላበት ጊዜ ገቢውን ለማግኘት የወጣና በግብር ከፋዩ የተከፈለ አስፈላጊ (necessary) የሆነ ወጪ ተቀናሽ የሚደረግ ሲሆን ይህም ወጪ የሚከተሉትን ይጨምራል፡-
ቤቱ ያረፈበት የመሬት ኪራይ (lease)፣
የጥገና ወጪ፣
የቤቱ፣ የቤት ዕቃዎችና የመሣሪያዎች የእርጅና ቅናሽ፣
ወለድና የመድን አረቦን፣
ታክስን ሳይጨምር ለመሬቱ ወይም ከተከራየው ቤት ጋር በተገናኘ ግብር ከፋዩ ለመንግስት ወይም ለከተማ አስተዳደር የከፈላቸው ክፍያዎች፣